በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በለንደን የሚኖሩ ሶማሊያውያን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ


የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን
የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን

ጋሻሞ በሚባለው የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ጂማዖ ዱብቲ በተባለች ከተማ ሃያ አንድ ሶማሊያውያን በኢትዮጲያ ፖሊሶች መገደላቸውን በመቃወም ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚኖሩ ሶማሊያውያን በትላንት ዕለት ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ከአሜሪካ ድምጽ የሶማሊኛ አገልግሎት የደረሰን ዜና አስታውቋል።

የሰልፉ ዓላማ በግድያው ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና ስለድንገቱ የኢትጵያ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ ለመጠየቅ መሆኑን ከሰልፉ ተካፋዮች አንዱ አሊ ሳአድ ዓብደልቃዲ ሲያስረዱ እ.አ.አ. ሰኔ 5 ቀን ጂማዎ ዱብቲ ውስጥ ስለተፈጸመው ፍጅት ተቃውሟችንን ለመግለጽ ነው። ያለነው ነጻ ሃገር ነው ስለዚህ የሚሰማንን እየተናገርን ነው ብለዋል።

ሳሃል ዩሱፍ የተባሉ ሌላ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ስለግድያው ማብራሪያ እንዲሰጥ በመጠየቅ የእቤቱታ ደብዳቤ ፈርመናል ደብዳቤውን ወደሄጉ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) እናቀርባለን ማለታቸውን ዘገባው አስታውቋል።

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)
የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)

ፋራህ ኣሊ የተባሉና በሰልፉ ለመካፈል ከበርሚንግሃም ወደለንደን መጓዛቸውን የገለጹ ተሳታፊ በበኩላቸው ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የትውልድ ከተማቸው መሆኑን ገልጸው ከተገደሉት መካከል ልጆች አረጋውያንና ነፍሰ ጡር ሴቶች አሉባቸው ብለዋል። በሮማዳን የመጀመሪያ ቀን የተፈጸውምን ጥቃት ያደረሱት የኢትዮጳያ ክልል አምስት ፖሊሶችና ልዩ ፖሊስ ሃይሎች ናቸው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በለንደን የሚኖሩ ሶማሊያውያን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:27 0:00

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ምላሽ ለማግኘት የሶማሊኛ ክፍል ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጿል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG