በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የሰው ህይወት ጠፋ


የሶማሊያ የፖሊስ ክፍል በገለጸው መሰረት አንድ አጥፍቶ ጠፊ ሞቃዲሾ በሚገኘው ዋርዳ ናባዳ ወረዳ በሚገኘ መሥርያ ቤት ላይ ዛሬ ባደረሰው ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለዋል።

በዋናው የወረዳው ጽህፈት ቤት የረመዳን ምግብ ይከፋፈል በነበረበት ወቅት አጥፍቶ ጠፊው በፈንጂ የተሞላ ቶዮታ መኪናን ነድቶ ገባበት ሲሉ እማኞች በአሜሪካ ድምጽ ላለው የሶማሊኛ ቋንቋ አግለግሎት ተናግረዋል።

ፖሊስ በፍንዳታው 9 ሰዎችቆስለዋል ሲል የዓይን ዕምናኞች ግን የቆሰሉት 30 ናቸው ብለዋል።

ዒላማ የተደረገው ህንፃ ቪላ ሶማልያ በተባለው በዋርታ ናባዳ ወረዳ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት አጠገብ ይገኛል።

ፅንፈኛው ቡድን ዐል ሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነት ውስዷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG