በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ የቦምብ ጥቃት ከተገደሉት የአሜሪካ ዜጋ ይገኛሉ

ሞቃዲሾ የቦምብ ጥቃት የቆሰሉ
ሞቃዲሾ የቦምብ ጥቃት የቆሰሉ

ባለፍው ቅዳሜ ሞቃዲሾ ውስጥ በደረሰው ከባድ የቦምብ ጥቃት ከተገደሉት በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መካከል አንዱ ዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ክፍለ ሃገር ብሎሚንግተን ከተማ ነዋሪ የነበሩ የአሜሪካ ዜጋ መሆናቸው ተገልፀ።

ባለፍው ቅዳሜ ሞቃዲሾ ውስጥ በደረሰው ከባድ የቦምብ ጥቃት ከተገደሉት በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መካከል አንዱ ዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ክፍለ ሃገር ብሎሚንግተን ከተማ ነዋሪ የነበሩ የአሜሪካ ዜጋ መሆናቸው ተገልፀ።

ከሃያ ዓመት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ የመጡት የሃምሳ እንድ ዓመቱ አህመድ አብደካሪም ኢዮው ያረፉበት የሞቃዲሾ ሆቴል እንዳሉ ነው በፍንዳታው የሞቱት።

ፍንዳታው የደረሰው ሶማሊያ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስራ ለማግኘት ሊሞክሩ ሞቃዲሾ በገቡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት በሰብዓዊ አገልግሎት ትምህርት ዲግሪያቸውን ያገኙት አብዲ ኢዮው ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG