በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያ ጋዜጠኞችን ማጥቃቱ ተባብሷል


በሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀሞድ አብዱላሂ መሀመድን በመቃወም እኤአ ሚያዝያ 25/ 2021 በሞቃድሾ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ
በሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀሞድ አብዱላሂ መሀመድን በመቃወም እኤአ ሚያዝያ 25/ 2021 በሞቃድሾ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ

የአፍሪካ ቀንድ አገር የሆነችው ሶማልያ ወደ ምርጫ እያመራች ባለችበት በዚህ ወቅት በአፍሪካ የፕሬስ ነጻነት ውስጥ፣ ሶማልያ የመጨረሻውን ደረጃ የያዘች መሆኑን የፕሬስ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል፡፡ የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ምክን ያት በማድረግ ባወጡት መግለጫ ፣ የሶማሊያ ባለሥልጣናት ለጋዜጠኞች መብት የበለጠ መስራት ይኖርባቸዋል በማለትም አሳስበዋል ፡፡

ባለፉት አራት ወራት የሶማልያ ባለሥልጣናት ሶስት የሚዲያ ተቋማትን በመውረር እስከ 30 የሚደርሱ ጋዜጠኞችን አስረዋል፡፡

ባለፈው መጋቢትም ፖሊስ ሁለት የሞቃዲሾ ጋዜጠኞችና ተመሳሳይ ሥራ ላይ በነበሩ ሌሎች ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ያቆሰላቸው መሆኑም ተመልክቷል፡፡

እንደ ሱማልያ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ቡድን ከሆነ ፣ እነዚህ ሁሉ ጥቃቶች የሚፈጸሙት በሶማልያ መንግሥት ብሄራዊ የደህንነት ተቋም እና ፖሊስ አማካይነት ነው፡፡

ቢሻር መሃመድ የሱፍ፣ የሙታቅባል ሬዲዮ አዘጋጅ ነው፡፡ ፖሊስ እኤአ ሚያዝያ 27 በጣቢያቸው ላይ ባደረገው ወረራ፣ የደረሰበት ስብራት እስካሁን ድረስ አብሮት ነው፡፡ በርካታ ንብረቶቹም የተወረሰበት መሆኑን ገልጿል፡፡

“ፖሊሲ ወደ ጋዜጠኞቹ ቢሮ ሰብሮ እንደገባ ግርፋትና ድብደባ ሳይደርስባቸው ሠራተኞቹ በሙሉ እጃቸውን እንዲሰጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡ ላፕቶፖችን ጨምሮ በርካታ የጣቢያውን ንብረት በፖሊስ የተወረሱ ሲሆን እስካሁን ድረስ ያልተመለሰላቸው መሆኑንም ተናግሯል፡፡

ሶማልያ ለጋዜጠኞች ምቹ ያልሆነችና እጅግ አደገኛ ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም እንደዚያው ናት፡፡ ባለፈው መጋቢት ወር በጋልካዮ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ለተገደለው ጋዜጠኛ ኃላፊነቱን አልሸባብ የተባለው ታጣቂ ቡድን ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

በሶማልያ ጋዜጠኞችን ማጥቃቱ ተባብሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

ይሁን እንጂ መች እና በምን መንገድ መካሄድ እንዳለበት፣ መግባባት ያልተደረሰበት ምርጫ፣ በጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ ጫና የፈጠረ ሲሆን ዛቻዎችንም አስከትሏል፡፡

አብደላ ሙአሚን የሶማልያ ጋዜጠኞች ተወካይ ዋና ጸሀፊ ነው፣ እንዲህ ይላል

“ጋዜጠኞች ላይ የሚካሄደው ጥቃትና ዛቻ እየጨመረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው በሶማልያ ይካሄዳል በተባለው ምርጫና እየተካሄድ ባለው ወሳኝ የሽግግር ወቅት የተነሳ ነው፡፡”

ሞአሚ እንደሚለው የሶማልያ ባለሥልጣናት በቀጠሯቸው ሰዎች አማካይነት፣ የፌስቡክ አድራሻዎችን እየፈተሹና በድረ ገጽ የሚወጡ ሪፖርቶችን እያከላከሉ ነው፡፡

አሁንም አብዱላ ሙአሚን እንዲህ ይላል

“ደረጃውን የጠበቀ የማህበረሰቡ አጠቃቀም በሚል ስለ ፌስቡክ አጠቃቀምና ይዘቱን ስለሚያቀናብረው ስርዐትም ቢሆን ጥርጣሬ አለን፡፡ ይህን ምክያት አድርገው ጋዜጠኞችን ለማፈንና በሶማልያ ጋዜጠኞች የሚቀርቡትንና ከአገር ቤት የሚወጡትን ገለልተኛ ዘገባዎች ለመገደብ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ጋዜጠኞችን በጣም እየጎዳ ነው፡፡ጋዜጠኞች ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ሆነ ፌስቡክ ላይ አንድ ዘገባ ሲያቀርቡ ይህንን ሆን ብለው የሚጠባበቁ የመንግሥት ሰዎች ዘገባዎቹን ከማህበራዊ ሚዲያው ገጽ ያጠፏቸዋል ወይም ሳንሱር ያደርጓቸዋል፡፡”

የሶማልያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሁሴን ሮቤል፣ ጽ/ቤት የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ፣ የሳቸው አስተዳደር፣ የሶማልያ ጋዜጠኞችን ሥራና ደህንነት ለመጠበቅና ለማሻሻል ፣ ጋዜጠኞች ከመንግሥት ተቋማትመረጃዎችን የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻት፣ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የሶማልያ ሚዲያዎችም ከሀሰተኛና ካልተጣሩ ወሬዎች በመቆጠብ፣ ለአገሪቱ ሰላምና ግንባታ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

ምርጫውን ተከትሎ ሊነሱ ለሚችሉ ሁከቶችም ጋዜጠኞቹ ምክንያት እንዳይሆኑ ጠይቋል፡፡

(ከሞቃዲሾ የቪኦኤ ዘጋቢ ሞሀመድ ካዬ ከላከው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG