በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓለማቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ እንደሚችሉ አስታወቁ

የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አብድቂያን ሳዒድ አራብ
የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አብድቂያን ሳዒድ አራብ

"የፀጥታው ሁኔታ ተሻሽሏልና፣ አሁን ዓለማቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ ይቻለናል" ሲሉ፣ የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አስታወቁ።

"የፀጥታው ሁኔታ ተሻሽሏልና፣ አሁን ዓለማቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ ይቻለናል" ሲሉ፣ የሶማልያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አስታወቁ።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት አብድቂያን ሳዒድ አራብ በተናገሩት ቃል፣ ሶማልያ አገሯ ላይ በራሷ ስታዲየም፣ እአአ ከመጪው 2018 ጀምሮ ዓለማቀፍ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን ማስተናገድ እንደምትችል ገልፀዋል።

"የጸጥታና የደኅንነት ስጋቱ በመሻሻሉ፣ ከእንግዲህ የአገራችንን ውድድሮች በራሳችን ስታዲየም ማካሄድ እንችላለን" ሲሉ የስፖርቱ ፕሬዚደንት መናገራቸው ተሰምቷል።

"የሶማልያ ሕዝብ ብሔራዊ ቡድኑ በራሱ ሜዳ ሲጫወት መመልከት ይፈልጋል» ያሉት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት አራብ፣ «አገራችን ወደፊት እየገፋች በመሄድ ላይ በመሆኗም ይህ ዛሬ ተፈጻሚ እንዲሆን እንሻለን" ሲሉም አመልክተዋል።

እንደ ምሳሌም፣ ከአንዳንድ የወዳጅነት ውድድሮች በኋላ፣ የምሥራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድርን ማስተናገድ ይቻላል ማለታቸውም ተደምጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG