በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ የፍትሕ ጉባዔ


ሞቃዲሾ
ሞቃዲሾ

ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ በሚስተዋሉ ቁልፍ እና አሳሳቢ በሆኑ የፍትሕ እና የሕግ የበላይነት ችግሮች ላይ ይመክራል የተባለ የፍትሕ ጉባዔ ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ ተጀምሯል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:05:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ በሚስተዋሉ ቁልፍ እና አሳሳቢ በሆኑ የፍትሕ እና የሕግ የበላይነት ችግሮች ላይ ይመክራል የተባለ የፍትሕ ጉባዔ ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ ተጀምሯል፡፡
ሃሰን ሼህ ማኅሙድ - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት
ሃሰን ሼህ ማኅሙድ - የሶማሊያ ፕሬዚዳንት

ይህንን ለአራት ቀናት ይዘልቃል የባለ ጉባዔ የከፈቱት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ ማኅሙድ ናቸው፡፡

በጉባዔው ላይ ለምክክር ከሚቀርቡት ጉዳዮች መካከል የፍትሕ ዘርፉ ተቋማት ግንባታ፣ ለብሔራዊ ዕርቅ፣ መግባባትና ሰላምን ለማነፅ የፍትሕ መዋቅርና አሠራር መሻሻልን እንደ ውጤታማ መሣሪያ መጠቀም፣ ሸሪዓና መደበኛ ሕጎችን አጣጥሞና አቀናጅቶ መሥራት ዋና ዋና የሚባሉ ናቸው፡፡

ይህ ጉባዔ ያነሣቸዋል የተባሉ አበይት ጉዳዮችና ዛሬ ሶማሊያ ያለችበት ሁኔታ “ግንባር ለግንባር የሚጋጩ ናቸው” ይላሉ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካሊፎርኒያ የሚኖሩት ሶማሊያዊ ፀሐፊና ተንታኝ ፋይሰል አብዲ ሮብሌ፡፡
ፋይሰል አብዲ ሮብሌ
ፋይሰል አብዲ ሮብሌ

በትንታኔአቸው መጀመሪያ ላይ “ከመጭዋ ሶማሊያ ግዙፍ ግዛቶች፣ ወም ክልሎች፣ ወይም ስቴቶች አንዷ የምትሆነው በኪስማዮ ማዕከልነት የምትቋቋመው ጁባላንድ ትሆናለች” ይላሉ፡፡

ይህ አካባቢ ደግሞ ከሞቃዲሾ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲህ የተለሣለሰና ቀላይ አይደለም - ይላሉ ፋይሰል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG