በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሃዮ የሶማሊያ ማኅበረሰብ መሪ መገናኛ ብዙሃንን አማረሩ


አብዱልራዛቅ አሊ
አብዱልራዛቅ አሊ

የዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዮ ክፍለ ግዛት ኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የደረሰው ጥቃት የእኛ ጥፋት አይደለም ሆኖም ግን ማኅበረሠባችን በዚያ ጥቃት ሰበብ ለጉዳት ይጋለጣል ብለን እንፈራለን ሲሉ ኮሉምበስ ኦሃዮ ያሉ የሶማሊያ ማህበረሰብ መሪዎች ስጋታቸውን ገለጡ ።

አብዱልራዛቅ አሊ የተባለው የአስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ሶማሊያዊ፣ ሰኞ ዕለት ያሽከረክር የነበረውን መኪና ቆመው በነበሩ ሰዎች ላይ እየነዳ ከወጣ በኋላ፣ ከመኪናው በመውረድ በስለት ወጋግቶ መግደል መጀመሩ ተዘግቧል፤ በወቅቱም ወጣቱ በፖሊስ በጥይት ተመቶ ተገድሏል፡፡

አብዱልራዛቅ እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም. ከቤተሰቡ ጋር ከሶማሊያ የተሰደደ፣ ሁለት ዓመት ፓኪስታን ኖሮ ወደ ዩናያትድ ስትቴትስ የመጣ መሆኑ ተገልጿል።

በኦሃዮ የሚኖሩ የሶማሊያ ማህበር ስራ አስኪያጅ ሀሰን ኦማር አጥቂው ምን እንዳነሳሣው ወዲያው ማወቅ አልቻልንም፤ ነገር ግን መገናኛ ብዙሃን ሶማሊያዊ ሁሉ መጥፎ እንደሆንን አድርገው ያቀርቡናል ሲሉ አማርረዋል።

ጥቃቱን እንደማህበረሰብ የፈፀምነው ይመስል ከኛ ጋር መያያዙን ስንሰማ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ቀን ዝም አልን። ልጆቻቸውን ከልጆቻችን ጋር አብረው የሚያስተመሩ ጎረቤቶቻችን፣ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ እና ሌሎችም በሥራ አጋጣሚ ሁሉ የመናገኛቸው ሠዎች ሁሉ ድርጊቱ የኛ ጥፋት አለመሆኑን ግን ወጥተን ስለጥቃቱ የሚሰማንን ተናግረን ማሳመን አለብን ብለን ተነስተናል ብለዋል፡፡

አብዛኛው የማኅበረሠባችን አባላት፣ በከተማዋ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩ ናቸው፤ አንድ ግለሰብ በፈፀመው አሰቃቂ ጥቃት ምክንያት፣ ግለሰቡ እኛ ከተወለድንበት ሀገር በመሆኑ ብቻ አንድ ላይ ልንደመር አይገባም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG