ዋሽንግተን ዲሲ —
በሶማልያ መዲና ሞቃድሾ፣ በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ የመንገድ ፍተሻ ኬላ ላይ፣ ዛሬ ቅዳሜ ፣ በአንድ የአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ፣ አንድ የፖሊስ አባልን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች ዘጠኝ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡
የሶማልያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ እንደተናገሩት ለፍተሻ ቆሞ ከነበረው ተሽከርካሪ የፈንዳው ቦምብ ሰባት ተሽከርካሪዎችና ሶስት ጋሪዎች መውደማቸውና በአካባቢው በርካታ ደም ፈሶ መታየቱን ገልጸዋል፡፡
ስለ ጥቃቱ እሳካሁን ኃላፊነት የወሰደ ባይኖርም የሶማልያን መንግሥት መገልበጥ የሚፈልገው አልሸባብ እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን አዘውትሮ እንደሚያደርስ ይታወቃል፡፡