በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ ጥቃት


ሶማልያ ውስጥ ለደረሱ ሁለት ፍንዳታዎች፣ እስላማዊው አክራሪ ቡድን አል-ሻባብ ኃላፊነቱን ወሰደ

ሽብርተኛው ቡድን እንዳስታወቀው፣ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው በሶማልያዋ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኘውና ንብረትነቱ የዱባይ የሆነው ወደብ አስተዳዳሪ፣ በአንደኛው ታጣቂ ተገድሏል።

ፓወል አንቶኒ ፎርሞሳ የተባሉት የወደቡ ሥራ-አስኪያጅ የተገደሉት፣ በአንድ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂ መሆኑን፣ ሙሐመድ ዳሄሪ የተባሉ የአካባቢው የደኅንነት ባለሥልጣን ለፈረንሳዩ ዜና አውታAFP-ገልጸዋል።

«ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው የእኛ ኃይል ነው» ያሉት የአል-ሻባብ ወታደራዊ ኦፔሬሽን ቃል-አቀባይ አብዲኣሲስ ዓቡ ሙሳብ «ቀደም ሲልን አስጠንቅቀን ነበር፣

ሰሚ ጆሮ ግን አላገኝንም» በማለት ለሮይተርስ ዜና ምንጭ ተናግረዋል።

«ጥቃቱ፣ የሶማልያን የኃይል ምንጭ በሚመዘብሩት ቅጥረኛ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ ሰፊ ዘመቻ አካል ነው» ሲል፣ አል-ሻባብ ተጨማሪ መግለጫ አውጥቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG