በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ወታደሮች በታችኛው ሸበሌ ቁልፍ ከተማ ከአልሻባብ አስለቀቁ


የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት ኃይሎች በመታገዝ በታችኛው ሸበሌ ክፍለ ግዛት አንዲት ስትራተጂያዊ ከተማ ከአልሸባብ ሃይሎች አስለቅቀው ተቆጣጥረዋል ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ

ኩንትዋሬ የምትባለው ከተማ ከሞቃዲሾ ሁለት መቶ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ታጣቂው ቡድን በመንግሥት ይዞታ ባሉ ከተሞች ላይ ጥቃት ለማካሄድ መነሻው አድርጎ ሲጠቀምባት የቆየች መሆንዋ ተመልክቷል

ያስለቀቁዋት ሃይሎች የቤት ለቤት አሰሳ አካሂደው ሰላሳ ሶስት ልጆችን ከአልሻባብ ታጣቂዎች እጅ ማስለቀቃቸውም ታውቋል

XS
SM
MD
LG