በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥቃት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች ሊያቋቁም ነው


የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች ጥቃት የተፈፀመባቸውን የክልሉን ልዩ ልዩ ብሔረሰብ ነዋሪዎች ለማቋቋም 100 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታወቀ፡፡

የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ፋታ ለአሜሪካ ድምፅ በተለይ እንዳስታወቁት ሄጎ በተባለ የወጣቶች አደረጃጀት አማካኝነት ከ4 ሺ በላይ ግለሰቦች ልዩ ልዩ ጥቃቶች ተፈፅሞባቸዋል፡፡

አሁን የሚደረገው ድጋፍም የፈረሱ ቤቶችን ለመጠገንና የወደሙ ንግዶችን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ብለዋል፡፡

ሐምሌ 28 ጥቃት የተፈፀመባቸውን ለመደገደፍ በበጎ ፈቃደኞች የተቋቋመው ማኅበር በክልሉ እርምጃ ደስተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥቃት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች ሊያቋቁም ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG