አዲሱ የሶማሊያ ኘሬዚዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃሙድ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የተቀበሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የእንኳን ደሕና መጡ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች እና ልዑኮቻቸው ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ ቀጣና እንዲሆን በትብብር መስራት እንደሚገባ ትኩረት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡
ሁለቱም ሀገራት ለቀጣናው አለመረጋጋት መንስዔ የሆኑ እንደ ግጭት እና ድርቅ የመሳሰሉ ፈተናዎችን በመጋፈጥ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።