የሶማሊያ ጦር ትናንት ባደረገው ጥቃት 100 የሚሆኑ የአል-ሻባብ ተዋጊዎችን መግደሉን አስታውቋል። የአይን እማኞች ከበድ ያለ ውጊያና የአየር ጥቃት እንደነበር ተናግረዋል።
የቪኦኤው ሞሃመድ ዳይሴን ከሞቃዲሹ እንደዘገበው፣ በሃገሪቱ ማዕከላዊ ግዛቶች በተወሰደው ጥቃት ከመቶ በላይ የአል-አባብ ተዋጊዎች ተገድለዋል።
በአል-ሻባብ ላይ ጥቃቱ የተደረገው በአካባቢው ሚሊሻዎች እገዛ እንደነበር የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አብዱላሂ አሊ ተናግረዋል።
ከባድ ውጊያና አል-ሸባብ ላይ ያነጣጣረ የአየር ጥቃት እንደተፈጸመ ለቪኦኤ በስልክ የተናገሩ ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
ባለፈው ሳምንት በሞቃዲሹ ሁለት በመኪና ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎች 120 ሰዎችን ገደለው ከ300 በላይ ማቁሰላቸው ይታወሳል።