No media source currently available
የጁባላንድ ኃይሎችና የሶማሊያ ጦር በኬንያ ድንበር የሚያደርጉትን ግጭት የኬንያ ማዕከላዊ መንግሥት ቁጥጥር እንዲያደርግ የማንደራ ግዛት አስተዳደር ጠየቁ። አስተዳዳሪዉ ዓሊ ሮባ በባለፈው ሰኞ በማንዴራ ግዛት ቅርብ ርቀት በተፈጠረዉ ግጭት 12 የኬንያ ዜጎች መቁሰላቸዉን፣ ከ100 በላይ ደግሞ ከቤት ንብረታቸዉ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።