በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሜሲ ኢንተር ማያሚን የመቀላቀል ውጥን


የእግር ኳስ ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ፣
የእግር ኳስ ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ፣

የእግር ኳስ ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ሜጀር ሊግ እግር ኳስ ክለብ፣ ኢንተር ማያሚን ለመቀላቀል እንዳሰበ አስታወቀ፡፡

ሜሲ ይህን ያስታወቀው፣ ከፈረንሳይ ሻምፒዮኑ፣ ፓሪስ ሴንተር ዥርሜን ጋራ መለያየቱን ባስታወቀበትና በሳዑዲ አረቢያ የቀረበለትን ዳጎስ ያለ ኮንትራክት በመሻር ነው፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ፣ ከፓሪስ ሴንተር ዥርሜን፣ የመሰናበቻ ጨዋታውን ያደረገው ሜሲ፣ ጉዳዩን ወደ ባርሴሎና ከመመለሱ ጋራ አያይዞት ነበር፡፡ ይኹን እንጂ፣ የስፔይኑ ክለብ ላላጊጋ፣ በሚመራበት የጨዋታ ፋይናንስ ሕግ መሠረት፣ ክለቡ እጁ እንደታሰረበት ተነግሯል፡፡

ሜሲ ዘሙንዶ፣ ዲፖርቲቮ ከተባለው የስፖርት ጋዜጣ ጋራ ባደረገው ቆይታ፣ ከማያሚ ጋር ስምምነቱን እያጠናቀቀ እንደኾነ አስታውቋል፡፡

ስለ ሜሲ ውሳኔ፣ አስተያየታቸውን የሰጡ የአርጀንቲና ደጋፊዎች፣ ሜሲ ሲሰጠን ከኖረው ደስታ አንጻር፣ አሁን እርሱ ደስ ያሰኘውን ነገር ማድረግ ይችላል፤ ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

“በግልጽ እንደሚታየው፣ የዓለም ዋንጫን ድል ካደረገ በኋላ፣ የሞያው መገባደጃ ይመስላል፤” ያሉት አርጀቲናውያን አድናቂዎቹ፣ “በርግጥ የፈለገውን ማድረግ ይችላል፤ ትልቁን ደስታ አጎናጽፎናል፤ ከዚኽ ሌላ ከሜሲ የምንፈልገው ምንድነው?” ሲሉ መልካሙን ተመኝተውለታል፡፡

ሜሲ በበኩሉ፣ ወደ ባርሴሎና የማይመለስ ከኾነ፣ አውሮፓን በመልቀቅና ከእይታ ውጭ በመኾን፣ ቀሪ ዘመኑን፣ ስለ ቤተሰቡ የበለጠ ማሰብ እንደሚፈልግ መናገሩ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG