በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍሎች በረዶና ከፍተኛ ነፋስ በቀላቀለ ወጅብ ተመቱ


በደቡብ ካሮላይና የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የቀረበው ይህ ምስል ዮርክ ካውንቲ ውስጥ በረዶ እና አይስ የተሸፈነው አውራ ጎዳና ሰራተኞች ሲጠራርጉ እሑድ እአአ ጥር 16/2022
በደቡብ ካሮላይና የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የቀረበው ይህ ምስል ዮርክ ካውንቲ ውስጥ በረዶ እና አይስ የተሸፈነው አውራ ጎዳና ሰራተኞች ሲጠራርጉ እሑድ እአአ ጥር 16/2022

ትናንት እሁድ የዩናይትድ ስቴትስን ደቡባዊ ምስራቅ ግዛት የመታውና ከፍተኛ ንፋስና በረዶ የቀላቀለው የክረምት ወጀብ ትልቅ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

ከፍተኛው ወጀብ ዛፎችን የገነዳደሰ፣ ጣራዎችን የነቃቀለ፣ መንገዶችን በስብርባሪዎች የሞላና ብርቱ ቅዝቃዜን ያስከተለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በአካባቢዎቹ የኃይል ስርጭትን ያወደመ ሲሆን፣ ከ260ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጆርጅያ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ደቡብ ካሮላይና ፍሎሪዳ ግዛቶች የሚገኙ ደንበኞችን ያለ መብራት ያስቀረ መሆኑም ተነገሯል፡፡

በሻርለት ዳግላስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ከ1ሺ 200 በላይ የእሁድ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን፣ አውሮፕላኑ ጣቢያው 90 ከመቶ የሚሆነው በረራዎቹ መቋረጣቸው ተመልክቷል፡፡

እንደ ኖርዝ ካሮላይናና ዌስት ቨርጂኒያ፣ ባሉ ግዛቶች ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 11 ኢንች ወይም 30 ሴንቲ ሜትር በረዶ መጣሉ ተነግሯል፡፡

በቨርጂኒያ ከእኩለ ሌሊት እስከ ለሰባት ሰዐት ሩብ ጉዳይ ባለው 45 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ብቻ 142 የትራፊክ አደጋዎች የተመዘገቡ ሲሆን 162 የሆኑ ተሽከርካሪዎች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG