No media source currently available
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማን ዞን የክልልነት ጥያቄ ለመመለስ ይከናወናል ተብሎ የነበረውን የህዝብ የውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ማስተላለፉን፤ የምርጫ አስፈፃሚዎችንም ቁጥር መቀነሱን አስታውቋል። የውሳኔ ህዝብ ሂደት ሁሉንም የሚያካትት ነፃና ፍትኃዊ እንዲሆንም በሁሉም ዘንድ ስምምነት እንዳለ ተገልጿል።