የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በአራት ዞኖችና በአንድ ከተማ አስተዳደር እንደሚዋቀር የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባዔ ፋንታዬ ከበደ አስታውቀዋል።
ከሁለት ዓመታት በፊት አሥረኛው ክልል ሆኖ የተመሠረተው ሲዳማ ዞኖቹን ሳያዋቅር የቆየ ሲሆን የአሁኑ አደረጃጀት ምጣኔኃብቱን ለማሳለጥ፣ አገልግሎቶችን በቅርበት ለማግኘትና ከፍተኛ ነው የሚባለውን ሥራ አጥነት ለመቀነስ ሊያግዝ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሌላ በኩል መዋቅሩ ጉቦን ለመሳሰሉ ብልሽቶች መንስኤ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አንዳንድ ምሁራን ለቪኦኤ ባካፈሉት ሃሳባቸው አስጠንቅቀዋል።