ዋሺንግተን ዲሲ —
የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ማክሰኞ፣ መጋቢት 8/2007 ዓ.ም በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ለተቀዳጀው ድል የቀኝ ክንፍ ፓርቲዎች ደጋፊ የሆኑ መራጮችን ማማለል መቻሉን ተንታኞች ተናግረዋል፡፡
ኔታንያሁ ጥምር መንግሥት እንዲመሠርቱ ግራ ዘመሙና አዲሱ የፓርላማው አረብ አባላት ቡድኖች ጥያቄ ሳያቀርቡላቸው አይቀርም ተብሏል፡፡
በምርጫው ውስጥ የተሣተፉ የየሻ አቲድ ሴንትሪስት ፓርቲ ተወካይ ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤል አቶ ሽሞን ሰለሞን ምርጫው እየተካሄደ ሳለ ከቪኦኤ ጋር ተነጋገርው ነበር፡፡
ስለእራሣቸውና ስለምርጫው ሂደት ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡