በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሼል አሜሪካ ውስጥ በናይጀሪያዊያን ተከሰሰ


ከአሜሪካ ውጭ ተሠርቷል ለተባለ ጥፋት አሜሪካዊ ያልሆነ ኩባንያ አሜሪካዊያን ባልሆኑ ከሣሾች አሜሪካ ውስጥ ዶሴ ተከፍቶበታል፡፡

ግዙፉ የነዳጅ ዘይት አሣሽና አልሚ ኩባንያ ሼል ናይጀሪያ ውስጥ ተፈፅመዋል ከተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተከስሶ ለፍርድ ሊቀርብ እንደሚችል ናይጀሪያዊያን የመብቶች ተሟጋቾችና ለኩባንያዎች በተጠያቂነት መያዝ የሚታገሉ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ብዙ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ግን በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ይሰማል፡፡

ሙግቱ የተከፈተው የሼልን አድራጎት ተቃውመው ሲታገሉ በ1995 ዓ.ም [በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር] በተገደሉ ተሟጋች ባለቤት ወ/ሮ ኤስቴር ኪዮቤል እና በሮያል ደች ሼል ኩባንያ መካከል ነው፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ተከፍቶ ከነበረ ተመሣሣይ የክስ ዶሴ ጋር በተያያዘ ሼል የ15 ተኩል ሚልዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍል ተፈርዶበት፤ ክፍያውን ፈፅሟል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG