ኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ግሽበቱ በ2.2 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ባላፈው መጋቢት ከነበረበት 34.7 ከመቶ በሚያዝያ ወር ወደ 36.6 ከመቶ መግባቱን ሮይተርስ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ቪኦኤ ያነጋገራቸው በደሴና ወልዲያ አካባቢ የሚኖሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም እየከበዳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባና ኦሮምያ የሚገኙ ሁለት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አቶ ስዩም ጫኔና አቶ ተሾመ ገመቹ መንግሥት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ አለበት ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ለሰላም ባልቆሙበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብቱም ሆነ የኑሮ ወድነቱ ሊሻሻል እንደማይችልም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
ነዋሪዎቹንና ባለሙያዎችን ያነጋገረው ደረጀ ደስታ ነው፡፡