ዋሺንግተን ዲሲ —
ሰኔ 27 በየዓመቱ በዩናይትድ ስቴትስ የሚከበረው የነፃነት ቀን በአሜሪካውያን ልብ ውስጥ ልዩ ሥፍራ አለው። በዘልማድ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች ተሰባስበው አብረው በመብላትና በመጠጣት እንዲሁም ርችቶችን በመተኮስ የዛሬይቱን ጁላይ 4 አሜሪካ እአአ በ1776የተገኘችበትን ቀን ያከብራሉ። ዕለቱን የዩናይትድ ስቴትስን ዲሞክራሲ ዳግም ሲያስተጋቡበት ቆይተዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በዚህች በፖለቲካ በተከፋፈለች ሃገር ውስጥ - ዲሞክራሲ ወለምታ እንደደረሰበት ጎልቶ እየታየ ነው። ሰዎችን የሚያግባቡ የጋራ መድረኮች እየራቁ - ሲናገሩ በቁጣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መታየታቸው እያደገ መጥቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ