በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ሴት የወርቅ ማዕድን ሠራተኞች ትልቁ ሸክም አርፎባቸዋል


የሴኔጋል ሴት የወርቅ ማዕድን ሠራተኞች ትልቁ ሸክም አርፎባቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

የሴኔጋል ሴት የወርቅ ማዕድን ሠራተኞች ትልቁ ሸክም አርፎባቸዋል

የወርቅ ማዕድን በሴነጋል ኢኮኖሚ ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታወል፡፡ ወርቁን ለማውጣትና ለማንጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ፣ ሥራ ላይ የሚውለው ኬሚካል አካባቢዎችንና የማዕድን ሠራተኞችን ጤና እየጎዳ ነው፡፡

ከማዕድን ፍለጋ ሠራተኞች ውስጥ፣ ከፊሎች የሚሆኑት ሴቶች፣ ራሳቸውንና ብዙ ጊዜ አብረዋቸው ይዘው የሚሄዷቸውን ልጆቻቸውን ጤንነት እየጎዳ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡

ሜታ በአስከፊ በሆነው የራስ ምታት የምትሰቃይ ሲሆን የ14 ዓመት ሴት ልጇ አዋ ደግሞ ማስታወስ እስከምትችለው ድረስ ረጅም ጊዜ ትስላለች፡፡

በሴንጋል ሩቅ ምስራቅ በማሊና ጊኒ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ኬዶጉ ውስጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ሠራተኛ ናት፡፡

ልክ እንደ ብዙዎቹ ማዕድን አውጭዎች ልጆችዋን ወደ ማዕድን ፍለጋው ሥፍራ ይዛ የምታመጣው በአሁን ድረስ ገና ልጅዋን ታጣበለች፡፡

እዚህ የመጣሁት ልሰራ አይደለም፡፡ እንዴት ነው በህይወት መቆየት የምችለው በምን እኖራለሁ?” ስትልም ትጠይቃለች፡፡

የኮዴጉ ወርቅ ማዕድን ፍለጋ አካባቢ ለልጆች የሚሆን ቦታ አይደለም፡፡

ብዙ ክፍት የሆኑ ስፍራዎችና ጉድጓዶች አሉ፡፡ የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች የሉም የማዕድን ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች የተጋለጡበት አቧራ የተመረዘ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

አዋ እና ሌሎች ህጻናት ልጆች በአካባቢው የሚጫወቱ ሲሆን የሚተኙትም ከትልቁ የማዕድን ፍለጋው ጉድጓድ ጥቂት እልፍ ብለው ነው፡፡

ይህን ስትገልጽ “ለበሽታው መጋለጥ የጀመረው በመጠጥ ውሃ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ የጉድጓድ ውሃው ተበክሏል፡፡ ንጹህ ዋሃ የለም፡፡ ይህን ውሃ በምትጣጠበት ጊዜ እንደምትታመም ታውቃለህ” ብላለች፡፡

ወርቁ አንዴ ከተሰበሰበ በኋላ ማዕድን አውጭዎቹ ሜሪኩሪ በመጠቀም ያቀልጡታል፡፡ ሜሪኩሪ ነርቮችን የሚያጠቃ ሲሆን የምግብ ማዋሃጃ እና የሰውነት የተፈጥሮ መከላከል ሥርዓትን ይጎዳል፡፡

ሳምባንና ኩላሊት የሚጎዳ ሲሆን፣ የመስማት ችሎታን፣ ሚዛን መጠበቅ፣ እይታን ማሰብንና መተንፈስን ይከለክላል፡፡ ከጉድለት ጋር መወለድንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

አንዳንዶቹ ሴት የማዕድን ፍለጋ ሠራተኞ የሚታይ የጤና ችግር አለባቸው፡፡

በኬዶጉ 98 ከመቶ የሚሆኑ ሴንጋላውያን ማዕድን ፍለጋ ሠራተኞች በዓመት ከአምስት ቶን በላይ ሜርኩሪን ይጠቀማሉ፡፡

ከወርቅ ምርት ሥራው የሚወጡ ኬሚካሎችም አካባቢውን ይበክላሉ፡፡

በኬዶጉ የወርቅ አውጭ ሠራተኞች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ማማዱ ድራሜ “ሜርኩሪው ከወርቅ እንዲለይ በሚደረግበት ጊዜ ወደ አካባቢው በመትነን ከዛፍ ቅጠሎች ጋር ይጣበቃል፡፡

ከዚያም በዝናብ ወይም በነፋስ ታጥቦ ወደ መሬት ዘልቆ ይወርድና አሳዎቹ ተጋላጭ ወደሚሆኑበት ወደ ወንዞች ይዘልቃል፡፡ በጣም ጉጂ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡” ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

በኬዶጉ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ሥራ የአፈር መሸርሸርና የደን መመናመንን እንደሚያስከትልም ተነገሯል፡፡

አብዛኞቹ የሴነጋል ባለሙያዎቹ ወይም በግላቸው የሚሰሩት ትናንሾቹ የወርቅ አውጭዎች ሠራተኞች የሚገኙት በኬዶጉ ግዛት ነው፡፡

ኢንደስትሪው ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ወሳኝ ሲሆን ለሠራተኞችም መተዳደሪያቸው ነው፡፡

እኤአ በ2020 የሴነጋል የወርቅ ማዕድን ሚኒስትርና ማዕድን ፍለጋ 400 የሚደርሱ ከሜርኩሪ ነጻ የሆኑ የወርቅ ማውጫ ፕሮጀክቶችን ዘርግተዋል፡፡

በሴነጋል የማዕድን ሚኒስትር የወርቅ አንጣሪዎችና የአነስተኛ ማዕድን ፈላጊዎች ዳይሬክተር የሆኑት አቡ ሶው “ወርቅ ለማንጠር ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ሰዎች በሙሉ ምንም ኬሚካል እንደማይጠቀሙ ያውቃሉ፡፡

ከማዕከሉ ውጭ ወርቆቻቸውን ለማንጠር ኬሚካል የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ገደብ መጣል የሚያስችለንን ደንብ እናወጣለን፡፡”

ይሁን እንጂ አሁን ግንባታው ገና መጀመሩ ሲሆን ሁለት ዓመታት ያህል እንደሚፈጅ ተናግረዋል፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን ወርቅ በማውጣት ሥራ ላይ የተሰማሩት እንደ የመሳሰሉት እነሱና ልጆቻቸውን መርዛማ ለሆኑ ንጥረ ነገሮች መጋለጣቸውን እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ፡፡

XS
SM
MD
LG