በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ም/ቤቱ የባይደንን የክትባት ውሳኔ ውድቅ አደረገ


የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ መወሰኛው ምክር ቤት፣ ፕሬዚዳንት ባይደን የኮቪድ-19ን ለመከላከል 100 እና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው የንግድ ድርጅቶች ሠራተኞቻችውን እንዲያሰከትቡ፣ ወይም በየሳምንቱ እንዲመረመሩ በሥራ ገበታ ላይ ማስክ እንዲያደርጉ ያወጡትን ትዕዛዝ የሚሽር ህግ ትናንት ረቡዕ አጸደቀ፡፡

52ለ48 በሆነ ድምጽ የተደረገው የፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ ዴሞክራቶችን ወደ ሚቆጣጠሩት ወደሌላኛው የተወካዮች ም/ቤት ያመራ ሲሆን በዚያ የማለፍ ዕድሉ የመነመነ ነው ተብሏል፡፡ ስለሆነም ምንም እንኳየ ባይደን ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ሊታይ የሚችል ሊሆን የሚችልበት እድል ቢኖርም ለጊዜው ግን በሥራ ሆኖ የሚቀጥ ልመሆኑን ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ግን ውሳኔውን ያሳለፉት የምክር ቤቱ አባላት የባይደን ውሳኔ በሃገሪቱ የንግድ ማኅበረሰብና ተጠቃሚው ህዝብ ላይ ፍርሃትና ስጋት የሚለቅ ነው በማለት ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG