በውጭ አገር የሚኖሩ የፓርቲው ደጋፊዎች እገዛ በመሻትና ተሳትፏቸውን ለማነቃቃት ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙ አንዲት ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢትዮጵያን የፖለቲካና ዲሞክራሲ ይዞታ ዙሪያ የሰነዘሩትን አስተያየት አስመልክቶም ቅሬታቸውን በጽሁፍ ጭምር ማቅረባቸውን አቶ ይልቃል አመልክተዋል።
የተባለውን አስተያየት የሰነዘሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሚንስትር በበኩላቸው ባገባደድነው አጋማሽ በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከዚያ አስቀድሞ በጋዜጣው ርዕሰ አንቀጽ ላይ የቀረባቸውን ትችት “ከተናገሩበት ጭብጥ ውጭ ነው የተወሰደው፤” ሲሉ ተከላክለዋል።
ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ ወደ ቢሯችን ጎራ ካሉት የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ሊቀ መንበር ጋር በእነኚህ እና ሌሎች ተዛማች ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረግነውን ሙሉ ቃለ ምልልስና ተያያዥ ዜና ከዚህ ያድምጡ።