በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲያትል ከተማ የደረሰ እሳት 5 ኢትዮጵያዊያንን ገደለ


ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራውን ቀጥሏል

ሶስት የመኝታ ክፍሎች ያሉት የባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ በእሳት መያያዙ ለፖሊስ የተገለጸው ጠዋት 4 ሰአት ላይ ነበር። በቤቱ ውስጥ የነበሩ ከ5 አመት እስከ 22 አመት የሚሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት--ከቃጠሎውና ከጭሱ ጋር በተያያዘ--ህይወታቸው አልፏል።

ፍሪሞንት በመባል በሚታወቀው ሰፈር የሚኖሩት ሄለን ገብረጊዮርጊስ በዚህ አደጋ ሶስት ልጆቻቸውን፣ ወንድማቸውንና እህታቸውን አጥተዋል። የሟች ቤተሰብን ወክለው ለአካባቢው ጋዜጦች የተናገሩት አቶ ዳንኤል ገብረጊዮርጊስ የ22 አመቷ እህታቸው እየሩሳሌም ገ/ጊዮርጊስ፣ የ13 አመቱ ዮሴፍ ገብረ-ጊዮርጊስ፣ የ5, 6እና 7 አመት ህጻናት ያሲን ሻማም፣ ነስሪን ሸማምና ነይላ ስሚዝ በአደጋው መሞታቸውን አስታውቀዋል።

የመገናኛ ብዙሃን የአይን እማኞችን ጠቅሰው እንደዘገቡት የሶስቱ ህጻናት እናት ሄለን ገብረ-መድህን አንድ ልጅ ይዘው በእሳት ከጋየው የመኖሪያ ህንጻ ወጥተዋል። “ልጆቼ ውስጥ ናቸው፣” ብለው ተመልሰው እንዳይገቡ በጎረቤቶቻቸው ተይዘው የእሳት አደጋ ተከላካይ ፖሊስ እስኪመጣ ምንም ማድረግ እንዳልተቻለ ታውቋል።

አስቀድሞ የመጣው የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ውሃ መርጨት ስላልቻለ ሌላ እንዲመጣ ተደርጎ በደቂቃዎች እሳቱን ማጥፋት እንደተቻለ ታውቋል። ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራውን ቀጥሏል።

ጉዳቱ የደረሰባቸው የቤተሰብ አባላት በቤት ውስት የነበሩትና የተረፉት ሁለቱ የመጀመሪያ ደረጃ ቀላል ህክምና አግኝተው በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG