በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መልስ ያላገኙት ብርቱ ጥያቄዎች እና ተሥፋ የተጣለበት ፍለጋ


ዶ/ር አሌክስ ዮሃንስ እና ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል
ዶ/ር አሌክስ ዮሃንስ እና ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል

አዎን! ዓለምን ክፉኛ ስላስጨነቀውና መላ ስላልተገኘለት በሽታ COVID 19 ነው የምናወራው። ከሳይንሱ ዓለም ውጭ ድንገት ከሁሉም አቅጣጫ የሚጎርፉ ከሚመስሉት “የይሆናል መላዎች” እና እንደፈቃድ ከሚሰነዘሩ የፈውስ ሃሳቦች ባሻገር ለመሆኑ በምርምሩ ጎራ ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመረኮዘው መድሃኒትና ክትባት ፍለጋ ጉዞ ምን ይመስላል? የትኞቹስ ተሥፋ ሰጪ ይሆኑ ይሆን?

የቫይረሱን ተፈጥሮና ጸባይ እንዲሁም እስካሁን በውል የሚታወቁትን መረጃዎች መሠረት ከሌላቸው መለየት ጨምሮ ከሁለት የመድሃኒት ቅመማና አገልግሎት ባለሞያዎች ጋር የተካሄደው ቃለ ምልልስ በጥናትና ሙከራ ላይ ያሉትን መድሃኒቶች፤ የመከላከያ ክትባቶች ምንነት እና ያሉበትን ደረጃ፤ እንዲሁም ቫይረሱ ወደ ሰውነውት ከገባ በኋላ የሚከሰተውን ሁኔታ ይመለከታል።

ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ መምሕር እና የፋርማሲ ኮሌጅ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው። ዶ/ር አሌክስ ዮሃንስ በዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ከፍተኛ የጥናት ባለ ሞያ ናቸው።

ተከታታይ ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ።

መልስ ያላገኙት ብርቱ ጥያቄዎች እና ያልተገታው ፍለጋ .. ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:04 0:00
መልስ ያላገኙት ብርቱ ጥያቄዎች እና ያልተገታው ፍለጋ .. ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:53 0:00


XS
SM
MD
LG