በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ 19 ማጠናከሪያ ክትባት


አንድ ዓለም አቀፍ የክትባት ባለሙያዎች ቡድን ትናንት ሰኞ ባወጣው ጥናታዊ ጽሁፍ፣ የኮቪድ 19ን ማጠናከሪያ ክትባትን ለጠቅላላው ህዝብ መስጠቱን ተቃውሟል፡፡

ዘ ላንሰንት በተባለው የህክምና መጽሄት ላይ የታተመው የባህክምና ባለሙያዎቹ ጽሁፍ፣ ይበልጥ ተላላፊ የሆነው የዴልታ ቫይረስ ዝርያ ከመኖሩ በቀር፣ አሁን በመላው ዓለም እየተሰጠው ያለው የኮቪድ 19 ከትባት፣ በተለይ ሆስፒታል ገብተው በሚታከሙ ህሙማን ላይ ጠንካራ የመካለከል ሥራ እየሠራ ነው ብሏል፡፡

ባለሙያዎቹ በጽሁፋቸው አሁን ያሉት ክትባቶች የተለየ ዝርያ ያላቸውን ቫይረሶች እንዲቋቋሙ ማጠናከር እንጂ፣ ሌላ አዲስ ክትባት መፍጠር ተመራጭ አይደለም ብለዋል፡፡

የአዲሱን ክትባት ማጠናከሪያ የመስጠት ሀሳብ እየተስፋፋ የመጣው ፣ የፋይዘር ክትባት ውጤታማነት፣ በተለይ ጠና ያለ እድሜ ባላቸው ላይ፣ የመከላከል አቅሙ እየቀነሰ መምጣቱን የሚገልጽ ከእስራኤል የወጣ አንድ ጥናት ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG