ሰዎች ለሰዎች የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት በጦርነትና በድርቅ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው አራት ክልሎች በ 300 ሚሊዮን ብር 16 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ዛሬ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ሥምምነት ተፈራረሟል፡፡
የት/ቤቶቹ ግንባታ በሁለት አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰባስቲያን ብራንዲስ ገልፀዋል፡፡ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ሲሻሻልም ድርጅቱ በክልሉ ት/ቤቶችን የመገንባት እቅድ እንዳለው ዶ/ር ሰባስቲያን ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው ከትግራይ ውጭ ባሉት ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ከ1ሺህ 300 በላይ ትምህርት ቤቶች መፍረሳቸውን ገልፀው፣ በመልሶ ግንባታው ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አምባሳደር አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴም በጦርነት የወደሙ ት/ቤቶችን ለመገንባት ሁሉም እገዛ ሊያደርግ ይገባል ብሏል፡፡