ሳዑዲ አረቢያ እና ኢራን፣ በቻይና ሸምጋይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የመስማማታቸውን ዜና በሚመለከት፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተንታኞች ልዩ ልዩ አስተያየት እየተሰማ ነው፡፡
አንዳንዶቹ፣ ዜናው ለሊባኖስ አዎንታዊ ሊኾን እንደሚችል ምናልባትም፣ የኢራን ተጽእኖ ከፍተኛ ለኾነባት ለየመንም ጭምር መልካም ዜና ሊኾን እንደሚችል ይገልጻሉ፡፡
ኢራን ከሳዑዲ ጋራ የተስማማችው፣ “አሁን ያለችበትን ውጥረት ለማብረድ ያህል ነው፤” በሚል በጥንቃቄ የሚመለከቱ ተንታኞችም አሉ፡፡