በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ከፕሬዚዳንት ትረምፕ ጋር በዋይት ኃውስ ናቸው

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ዛሬ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር በዋይት ኃውስ ይገናኛሉ። የልዑሉ የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት የሚያደርጉት በሃገራቸውና የኢራን ውጥረት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ነው።

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ዛሬ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር በዋይት ኃውስ ይገናኛሉ። የልዑሉ የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት የሚያደርጉት በሃገራቸውና የኢራን ውጥረት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ነው።

የእርሳቸው ጉብኝት ጉዳዮቹን ለማንቀሳቀስና ኢራን የአካባቢውን መረጋጋት ለማደፍረስ ስለምትፈፅመው ተግባር ለመወያየት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዋይት ኃውስ ባለሥልጣን ተናግረዋል።

ሞሃመድ ቢን ሳልማን ወደዩናይትድ ስቴትስ የሚመጡት የአዲስቱ ሳዑዲ አረብያ ራዕያቸውን ለማስተዋወቅ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሲያነጋግሯቸው በደምብ እንደሚቀበሏቸው ይጠበቃል።

ሚስተር ትረምፕ የሱኒዎቹ ንጉሳዊ አስተዳደር ከሺያ መራሽዋ ኢራን ጋር ባላቸው ፉክክር በግልፅ ከነሱ ጎን መቆማቸው ሲታወስ የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ይህን አጋጣሚ ሊጠቀሙበት የቸኮሉ ይመስላል።

አልጋ ወራሹ ለሲቢኤስ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃል መጠይቅ የኢራኑን መሪ ከሂትለር ጋር ያወዳደሩ ሲሆን ኢራን ኒውክሊየር መሳሪያ ከሰራች ሳዑዲም ፈጥና ትቀጥላለች ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG