በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ አረቢያ ኢራንን ከሰሰች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኢራን፣ የአልቃይዳ ዋነኛ የሥራ አመራር የሆትን ሰዎች አስጠልላለች በማለት ሳዑዲ አረቢያ ክስ አሰማች።

ኢራን፣ የአልቃይዳ ዋነኛ የሥራ አመራር የሆትን ሰዎች አስጠልላለች በማለት ሳዑዲ አረቢያ ክስ አሰማች።

ሳዑዲ በተጨማሪም፣ ባለፈው ሳምንት 27 የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ለሞቱበት የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የሪያድ እጅ አለበት ተብሎ የቀረበባትንም ክስ አስተባብላለች።

ጎረቤት ፓኪስታንን እየጎበኙ ያሉት የሳዑዲው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አደል ቢን አህመድ አል ጁበር ናቸው ክሱንና ማስተባበያውን ዛሬ ያቀረቡት።

ኢራን፣ ከ9/11 የሽብር ጥቃት ጀምሮ የኦሳማ ቢን ላደንን ልጅ ጨምራ፣ ዋና ዋናዎቹን የአልቃይዳን የሽብር መሪዎች ታስጠልል እንደነበር የተናገሩት የሳዑዲው ሚኒስትር፣ "ኢራን የዓለማችን ዋናዋ የሽብርተኛነት ደጋፊነች" ብለዋል።

ሚኒስትሩ አል ጁበር ይህን የተናገሩት፣ ከፓኪስታኑ አቻቸው ሼህ ሙሐመድ ኩራሼ ጋር ኢስላ ማባድ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG