ሳዑዲ አረብያ ከኮቪድ ወዲህ ከፍተኛውን የሃጅ ተጓዦች እያስተናገደች ነው።
አንድ ሚሊየን የሚሆኑ የሃጅ ተጓዦች ለዘንድሮው የመስዋዕት በዓል፤ ኢድ አል አድሃ ቅድስቲቱ ከተማ መካ መግባታቸው የተነገረው በኮቪድ 19 ምክንያት ሃገሪቱ ድንበሮቿን ዘግታ ከቆየች ከሁለት ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው።
ከሦስት ዓመታት በፊት ለነበረው ኢድ መካ በሁለት ሚሊየን ተኩል ሙስሊም ምዕመናን ተጨናንቃ የነበረ ሲሆን በዓመቱ በ2012 ዓ.ም. ወረርሽኙ በዓለም ዙሪያ እጅግ ከፍቶ የነበረ ጊዜ በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙ የተፈቀደላቸው አሥር ሺህ የሚሆኑ የሳዑዲ አረብያ ነዋሪዎች ብቻ እንደነበሩ ይታወሳል።
ባላፈው ዓመት ወደ ስድሣ ሺህ የሚሆኑ የተከተቡ የሳዑዲ አረቢያ ነዋሪዎች ብቻ እንዲካፈሉ መደረጉም ተዘግቧል።
በዚህ ዓመት ለአምስት ቀናት በሚቆየው የሐጅ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ሳዑዲ አረብያ እንዲገቡ የፈቀደችላቸው ዓለምአቀፍ ተጓዦች ቁጥር 850 ሺህ መሆናቸው ታውቋል።
የኮቪድን መዛመት ለመቆጣጠር ሲባል ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ከመነገሩ ውጭ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንዳልተጣለ ተገልጿል።