በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የንግድ ልውውጥ ፕሮግራሟን እያጤነች መኾኑ ደቡብ አፍሪቃውያን ነጋዴዎችን አሳስቧል


አሜሪካ የንግድ ልውውጥ ፕሮግራሟን እያጤነች መኾኑ ደቡብ አፍሪቃውያን ነጋዴዎችን አሳስቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ፕሮግራሟን እያጤነች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ የደቡብ አፍሪቃ የንግድ ሰዎች ሐሳብ ገብቷቸዋል።

የደቡብ አፍሪካ የንግድ ቡድኖች፣ አገራቸው፥ ምርቶቿን በዩናይትድ ስቴትስ ገበያ፣ ከቀረጥ ነፃ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕድል እንዳትገፈፍ ለማድረግ፣ መንግሥታቸው ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲያደርግ እየገፋፉ ነው።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት እንደራሴዎች ቡድን በበኩሉ፣ ፕሪቶርያ ከሞስኮ ጋራ ያላትን ግንኙነት በመጥቀስ፣ በአፍሪካ የእድገት እና የንግድ ተጠቃሚነት ዕድል ሕግ መሠረት፣ የደቡብ አፍሪቃን በዕድሉ ተጠቃሚነት መቀጠል አስመልክቶ ጥያቄ አቅርቧል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ በዩክሬን ላይ ወረራ የፈጸሙና በዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት የሚፈለጉ ቢኾኑም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ በነሐሴ ወር ለሚካሔደው የመሪዎች ጉባኤ እንዲሳተፉ ጋብዛቸዋለች።

ኬት ባርትሌት ከጆሃንስበርግ ያጠናቀችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG