በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪው በደቡብ አፍሪካ ተያዘ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ኹለት ሺሕ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል፤ በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ፣ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን፣ የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ፣ ከሦስት ዓመት በፊት፣ በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚኾኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG