በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩዋንዳ የዘር ፍጅት የመጨርሻዎቹ ሁለት ተፈላጊዎች መሞታቸው ተረጋገጠ

በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩ የመጨረሻው ሁለት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተከሳሾች መሞታቸውን ማረጋገጡን በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ችሎት ትላንት አስታውቋል።

ርያንዱካዮ በሚል ስም ብቻ የሚጠራው እና ቻርለስ ሲኩብዋቦ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጉዳይ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ችሎት ሲፈለጉ የነበሩ የመጨረሻዎቹ ተከሳሾች መሆናቸውም ታውቋል።

በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም ከ1ሺሕ በላይ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው።

ሁለቱ ግለሰቦች 800 ሺሕ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁትዎችን በጨረሰው የዘር ፍጅት ላይ ተሳትፎ አላቸው በሚል ለሩዋንዳ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በ እ.አ.አ 1995 ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

ሲኩብዋቦ በእ.አ.አ 1998 በቻድ መሞቱን እና በዛው መቀበሩን እንዲሁም ርያንዱካዮ ደግሞ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሸሸ በኋላ ከዛም ወደ ዛየር ተሻግሮ ኪንሻሳ ላይ በ1998 ሕይወቱ ማለፉን ፍ/ቤቱ አስታውቋል።

በሩዋንዳው የዘር ፍጅት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሲፈለጉ የነበሩ ተከሳሾች ሁሉ መለየታቸውንም ችሎቱ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG