በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰርጌ ላቭሮቭ ከዚምባብዌ ጋር የኢኮኖሚ ስምምነት ተፈራረሙ


የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ
የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከዚምባብዌ ጋር የኢኮኖሚ ስምምነት ተፈራረሙ፣ ግንኙነታቸውንም አጠናከሩ።

የሩስያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከዚምባብዌ ጋር የኢኮኖሚ ስምምነት ተፈራረሙ፣ ግንኙነታቸውንም አጠናከሩ።

ሚንስትሩ፣ የቀድሞዋ ሶቭዬት ወዳጅ አገሮችን ኢትዮጵያን፣ ሞዛምቢክንና አንጎላን ጨምሮ በሚያደርጓቸው አምስት የአፍሪካ አገሮች ጉብኝታቸው ነው ዚምባብዌ ጎራ ያሉት።

ሰርጌ ላቭሮቭ በዛሬው የሀራሬ ጉብኝታቸው በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ሦስት የትብብር ስምምነቶችን የፈረሙ ሲሆን፣ ይህ ጉብኝታቸው፣ ከአሜሪካው አቻቸው የአፍሪካ የመጀመሪያ ጉዞ ጋር መገጣጠሙም ታውቋል።

በአንደበተ ርቱዕነታቸው የሚታወቁት ላቭሮቭ በዚሁ ጊዜ፣ በዚምባብዌ ሰብዓዊ መብት ረገጣና ሌሎችም ጭቆናዎች ይፈፅማሉ በሚል ዩናይትድ ስቴትስ በዚያች አገር ላይ የጣለችውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ በሂስ ጠርበዋል።

ላቭሮቭ በተጨማሪም፣ ቻይና አፍሪካ ውስጥ ያላትን ሚና በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲሌርሴን አመለካከት ነቅፈዋል። ቲለርሰን በሰጡት አስተያየት፣ ቻይና አፍሪካ ውስጥ ጥገኝነትን ታበረታታለች በማለት መንቀፋቸው ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG