በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን የቻይናውን መሪ ተቀበሉ


የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያላቸውን የጠበቀ ትስስር ለማሳየት በሞስኮ የሦስት ቀናት ጉብኝታቸውን ዛሬ ሰኞ ጀምረዋል፡፡

ሁለቱም አገሮች ማለትም ሩሲያና ቻይና፣ ከምዕራቡ ዓለም ተጋረጠባቸውን ችግር ፊት ተባብረው ለመቋቋም መጓጓታቸው ተነግሯል፡፡

የዚህ ሳምንቱ የቻይናው ፕሬዚዳንት ጉብኘት ዋና ዓላማ ቤጂንግ ሞስኮ በዩክሬን ያላትን ጦርነት ለመደገፍና ቻይና ለሁለቱም አገሮ ያቀረበቸውን የሰላም እቅድ አስመልክቶ ነው፡፡

በተለይ ቻይና ያቀረበችው የሰላም እቅድ ለቻይና ለራሷ በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርስቲ የሩሲያና ቻይና ግንኙነት ጠበብት የሆኑት ፕሮፌሰር አሌክሲ ማስሎቭ “በጉዳዩ ላይ በጣም ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየችው ቻይና ናት፡፡ ምክንያቱም የሚጠቅማት ነገር አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ ትስስሯ፣ ዓለም አቀፍ ንግድ፣ አቅርቦት እና መሠረተ ልማቷን አናግቷል፡፡ ቻያና በከፍተኛ ጫና ውስጥ ናት” ባይ ናቸው፡፡

ሁለቱም፣ ቤጂንግ እና ሞስኮ፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ትኩረት ያደረጉት በዩክሬን ሰላም እንዲመጣ የማዕቀቦችን መነሳት አስፈላጊነት ነው፡፡ ይህ በሞስኮ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መንከስ መጀመሩን ያሳያል ተብሏል፡፡

ባለሙያዎች ሩሲያ አሁን ካለችበት ማዕቀብ ውስጥ ለመውጣት የምትፈልገውን ያህል ቻይናም እንዲሁ ለመውጣት ትፈልጋለች ይላሉ፡፡

“ሩሲያና ቻይና ከምዕራቡ የማዕቀብ ጫና ስር ናቸው፡፡” የሚሉት፣ በሩሲያ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክር ቤት ተቋም ድሬክተር አንድሬ ኮርቹኖቭ “በርግጥ ሩሲያ ከቻይና በላይ በዚህ ማ ዕቀብ እጅግ ተጎድታለች ይሁን እንጂ ቻይናም ቢሆን ይህ ማእቀብ የሚያሳስባት ነው፡፡” ይላሉ፡፡

ከሚወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል የቻይናና ሩሲያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር የተፋጠጡባቸውን የመልክዓ ምድራዊ ጉዳዮችና በዚያ ረገድ ቤጂንግ ለሞስኮ ልትሰጥ ስለምትችለው ድጋፍ እንደሚገኝበት ተገምቷል፡፡

በተለይም አሁን፣ “ቻይና ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን ልትሰጥ ትችላለች” የሚለውን ግምት የዩናይትድ ስቴትስ ታምናለች፡፡

የሩሲያ ባለሙያዎች ግን ይህ የማይመስል ነገር መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በሩሲያ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክር ቤት ተቋም ድሬክተር አንድሬ ኮርቹኖቭ ስለዚሁ ሲናገሩ፣ “እኔ እንደሚመስለኝ ሩሲያ እንዲህ ያለውን ጥያቄ ለቻይና የማቅረቧ ነገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ሩሲያ በአገር ውስጥ ሀብት ልታሟላው የማትችለው የከባድ መሳሪያ እጥረት አለ ብዬ አላምንም” ብለዋል፡፡

በሞስኮ እና በቤጂንግ መካከል ያለው ግንኙነት ግን ፍጹም ነው ማለት አይደለም፡፡

ምንም እንኳ ሁለቱም አገሮች የበለጠ ትኩረት የሚሰሰጡት የጋራ ጠላት ቢኖራቸውም በማዕከላዊ እስያ የበላይነትን ለመያዝ እየተፎካከሩ ነው፡፡

“በርግጥ በአገሮቹ መካከል አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡” የሚሉት በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርስቲ አሌክሲ ማስሎቭ “በተለይ በማዕከላዊ እስያ ክልል ያላቸው ግንኙነትና በሩቅ ምስራቅ አገሮች ያለውን ሀብት በማልማት በኩል፣” ችግር ያለባቸው መሆኑን ገልጸው “ሁለቱም፣ ሩሲያና ቻያና፣ የበለጠ ግብ ስላላቸው እነሱን እንዴት መርሳት እንዳለባቸው ተለማምደዋል፡፡” ብለዋል፡፡

የቻይናው መሪ ጉብኝት፣ በሩሲያው የዩክሬን ወረራ ሳቢያ በደረሰው መነጠልና ማዕቀብ የተመቱ ሁለቱ አገሮች ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር በሚዛን እንዴት እንደሚቀመጡ የሚለኩበት አጋጣሚ ይሆናል ተብሎ ተጠብቋል፡፡

XS
SM
MD
LG