በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊዎች አዛዥ ነበርኩ" ያለ ሰው ከዩክሬን አምልጦ ኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት ጠየቀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዋግነር ግሩፕ የተባለው የሩሲያው የግል የቅጥር ተዋጊዎች አሰማሪ ኩባኒያ የተዋጊ አዛዥ ነበርኩ ያለ በዩክሬን ጦርነት የተካፈለ አንድ ግለሰብ አምልጦ ኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቁ ተገለጠ።

ሰውየውን የኖርዌይ የድንበር ጥበቃ አባላት ባለፈው ዐርብ ሀገሪቱን ከሩሲያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ እንዳሰሩት የኖርዌይ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የአንድሬ ሜድቪየዴቭ ጠበቃ በሰጡት ቃል እንዳሉት ከሆነ ኖርዌይ ጥገኝነት እንድትሰጠው ይፈልጋል።

"ለጦር ወንጀል መርማሪዎች ስለዩክሬኑ ውጊያ ተሞክሮው ለመናገርም ዝግጁ ነው" ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ቅዳሜ ዕለት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ በሲቪሎች መኖሪያ ህንጻ ላይ በደረሰው የሚሳይል ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ትናንት ሰኞ በዕለታዊ የምሽት መግለጫቸው ዲኒፕሮ ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራቸው ስለሚሰጣት የጦር መሳሪያ ድጋፍ በፍጥነት የተቀናጀ ውሳኔ ሊሰጥበት እንደሚገባ የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል።

በተያያዘ ዜና የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን የፊታችን ዐርብ ለዩክሬን ስለሚሰጥ ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ የሚነጋገር የአጋሮች ስብሰባ ጀርመን ውስጥ በሚገኝ የጦር ሰፈር እንደሚያስተናግዱ ታውቋል።

በሌላ በኩል "በጦር ወንጀል ፈጻሚነት የሚፈለጉ የሩስያ መሪዎች የሚጠየቁበት ልዩ ፍርድ ቤት መቋቋ አለበት" ሲሉ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቢርቦክ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG