በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መድረክ ከድርድሩ ራሱን አገለለ


ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር
ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር

"ድርድሩ ከተቀሩት ተቃዋሚዎች ጋር ይቀጥላል" - የኢህአዴግ ድርጅታዊ መሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

በኢትዮጵያ መንግሥትና ሃያ አንድ ብሔራዊ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ከሚካሄደው የቅድመ ድርድር ሂደት ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ መድረክ እራሱን አገለለ።

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ እንዳብራሩት መድረክ በቁጥጥር ሥር የሚገኙ አመራር አባላቱ እንዲፈቱና በመሪ ተደራዳሪነት በውይይቱ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥሪ ምላሻ ባለማግኘቱ፤ ከጠረጴዛው መነሳታቸውን ገልፀዋል።

ስድሥት ተቃዋሚ ድርጅቶች አዲስ የመሠረቱት ሌላ ጥምረትም፤ ኢሕአዴግ አደራዳሪ አልሰየመም ሲሉ ወንበራቸውን ስበው፤ ወረቀታቸውን ሰብስበው ከድርድሩ ለመነሳት ያላቸውን አዝማሚያ አስረድተዋል።

የኢህአዴግ ድርጅታዊ መሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፤ ድርድሩ ከተቀሩት ተቃዋሚዎች ጋር ይቀጥላል ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

መድረክ ከድርድሩ ራሱን አገለለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG