በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባግዳድ በሮኬቶች ተመታች


የኢራቅ ፀጥታ ኃይሎች ባግዳድ ወደ አረንጓዴው ዞን ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ዘግተውታል፣ እአአ 10/13/2022
የኢራቅ ፀጥታ ኃይሎች ባግዳድ ወደ አረንጓዴው ዞን ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ዘግተውታል፣ እአአ 10/13/2022

ኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበትና አረንጓዴው ዞን ተብሎ በተከለለው ሥፍራ ዛሬ ሀሙስ 9 ሮኬቶች ማረፋቸውን የኢራቅ ጦር አስታወቀ፡፡

ጥቃቱ የተሰነዘረው የኢራቅ ህግ አውጭዎች አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በተሰበሰቡበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የደህንነት ባለሥልጣናት በጥቃቱ አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን ሲገልጹ ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አልተገኘም፡፡

ባላፈው ወር የምክር ቤት አባላት፣ አፈ ጉባኤቸውን ለመምረጥ ተሰብሰበው በነበረበት ወቅትም አረንጓዴው ዞን ተብሎ የተከለለውን ሥፍራ ዒላማ ያደረጉ ሮኬቶች መተኮሳቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG