በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ላይ የደረሰው የሮኬት ጥቃት ተወገዘ


ዩናይትድ ስቴትስ ህወሓት በኤርትራ ላይ ያደረሰውን የሮኬት ጥቃት እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ የያዘውን ጥረት እንደምታወግዝ አስታውቃለች።

የትግራይ ክልል ኃይሎች አስመራ ላይ ያደረሱትን የሮኬት ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ "ምክንያት አልባ” ስትል አውግዛዋለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ትናንት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የሲቪሎች ደኅንነት እንዲጠበቅ፤ ውጥረቱ እንዲረግብ እና ሰላም እንዲመለስ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰባችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የትግራይ ክልል መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ቅዳሜ ኃይሎቻቸው አስመራ ላይ የሮኬት ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረው ጥቃቱ ይቀጥላል ሲሉ መዛታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG