በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በቦስተን ማርቶን ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በሁለቱ ወንድማማቾች Dzhokhar እና Tamerlan Tsarnaev ከደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ “ለመርማሪዎች ዋሽቷል፤” በሚል ተወንጅሎ ለሳምንታት ጉዳዩ ሲታይ የቆየው ሮቤል ፊሊጶስ በሁለት ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነ።
የከሳሽ አቃቤ ኅግና የተከሳሹ ሮቤል ፊልጶስ የኅግ ጠበቆች ለሁለት ሳምንታት ያቀረቧቸውን መከራከሪያዎች የሰማውና አሥራ ሁለት ሠዎች ያሉበት ለዳኝነቱ ከነዋሪው ሕዝብ የተመረጠው ቡድን በዛሬው እለት ብያኔውን ለችሎቱ አሰምቷል።
ብያኔውንና ቀጣዩን ሂደት በተመለከተ የተከሳሹን ዋና ጠበቃ አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶን አነጋግረናል።