ፈይሳ ይህን ምልክት ለምን እንዳሳየ ከአሜሪካ ድምጽ ተጠይቆም፤ “በሀገሬ ትልቅ ችግር አለ። መንግሥትን መቃወም አደገኛ ነው። ሰዎች እየተገደሉና እየታሠሩ ነው። ከተማሪነት ጀምሮ ይህን እያየሁ ነው። ነፃነት የለም። ለረጅም ጊዜ በውስጤ የታመቀ ስሜት ነው ፈንቅሎ የወጣው። በዚህ ድርጊት ሕዝቤን ነፃ አወጣለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝም የሚደረገውን ጭቆና ግን ለዓለም ማኅበረሰብ እንዳሳይበት ይረዳኛል። ከዚህ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ አልመለስም ብመለስ እታሠራለሁ “ ብሏል።
ከዚህ ቀጥሎ አነጋጋሪ እየሆነ የመጣው ፈይሳ ይህን ምልክት ያሳየው የፖለቲካና የኃይማኖት መልዕክት ማስተላለፍ በማይቻልበት የስፖርት መድረክ ላይ በመሆኑ መዳሊያውን ሊቀማ ይችላል፤ ቅጣትም ሊጠብቀው ይችላል የሚል አስተያየት ይሰጣል።
ፈይሳ ይህን ተጠይቆ ነበር።
አትሌቱ አሁን በሪዮ ይገኛል ቀጣይ ሕይወቱን በተመለከተ ሁኔታውን ነገሮችን የሚያስተካክሉለት ሦስት ሰዎች ሬዮ መግባታቸውንና 91 ሺሕ ዶላር መሰብሰቡን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት ዶ/ር ሰለሞን አንጋሼ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።