በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱጃሩ ሪቻርድ ብራንሰን በራሳቸው መንኮራኩር ወደ ህዋ መጠቁ


Virgin
Virgin

አዳዲስ የሚያስፈነጥዙ ነገሮችን ለመሞከር በመድፈር የሚታወቁት እንግሊዛዊው ባለብዙ ቢሊዮን ከበርቴ ሪቻርድ ብራንሰን እስከዛሬ ካደረጉት ሁሉ በበለጠ ድፍረት በተነሱበት ርምጃቸው ዛሬ ዕሁድ በራሳቸው መንኮራኩር ወደጠፈር መጥቀዋል።

የሰባ አንድ ዐመቱ ሰር ሪቻርድ ብራንሰን በዛሬ ጉዞአቸው በዚህ ተልዕኮ የሚፎካከሯቸውን ሌላውን ባለብዙ ቢሊዮን ባለጸጋ ጄፍ ቤዞስን ቀድመዋቸዋል። ቤዞስ ከዘጠኝ ቀናት በኋላ እሳቸውም በራሳቸው መንኮራኩር ወደህዋው ሊጓዙ እየተዘጋጁ ናቸው።

መንኮራኩሯን መሃል ላይ የያዘችውባለሁለት አካል አውሮፕላን ስትነሳ ሪቻርድ ብራንሰንን እና የጠፈር ጉዞ ኩባኒያቸው "ቨርጂን ጌላክቲክስ" አምስት ጠፈርተኞች ወደ አምስት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ተገኝተው ሸኝተዋቸዋል።


ከዚያም ወደ አስራ ሶስት ኪሎሜትር የሚጠጋ ከፍታ ላይ ሲደርሱ እነ ብራንሰንን የያዘችው መንኮራኩር ተነጥላ የራሷን ሞተር በመቀስቀስ ሰማኒያ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት በመንጎድ የጠፈሩን ወሰን ለመድረስ ችላለች።


የዚህ አጭር ደርሶ መልስ ጉዞ ዓላማ የሪቻርድ ብራንሰን "ቨርጂን ጌላክቲክስ" ኩባኒያ በሚቀጥለው ዓመት ሰዎች በክፍያ ለጠፈር ሽርሽር ለመውሰድ ያለው ዕቅድ አስተማማኝ መሆኑን ለማሳየት እንደሆነ ተገልጿል።


ብራንሰን እ አ አ በ2004 ዐመተ ምህረት ባቋቋሙት ቨርጂን ጌላክቲክስ አማካይነት የጠፈር ሽርሽር ለማድረግ ተመዝግበው የሚጠባበቁት ሰዎች ቁጥር ከስድስት መቶ ማለፉን አሶሲየትድ ፕረስ ያጠናቀረው ዘገባ አውስቷል።

XS
SM
MD
LG