በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐዲስ አበባ ዙሪያ ተፈናቃዮች “አድልዎ የተሞላበትና ማንነትን የለየ” ያሉትን ቤት ፈረሳ አማረሩ


የዐዲስ አበባ ዙሪያ ተፈናቃዮች “አድልዎ የተሞላበትና ማንነትን የለየ” ያሉትን ቤት ፈረሳ አማረሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00

በዐዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ፣ ለዓመታት ጎጆ ቀልሰው ከኖሩበት ቤታቸው፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ “ሕገ ወጥ ናችኹ፤” በሚል እንደተፈናቀሉ፣ ቤታቸው ፈርሶ እና ንብረታቸው ተበትኖ ባዷቸውን መቅረታቸውን ነዋሪዎች አማረሩ።

በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች፣ በሕጋዊ ውል የገዟቸውን ቤቶች ጨምሮ፣ የአካባቢው አስተዳደር በሚያውቀው ኹኔታ የገነቧቸው ቤቶች፣ በግብረ ኃይል እንዲፈርሱ በመደረጋቸው ለችግር መጋለጣቸውንም፣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። የማፍረሱ ሒደት፥ “አድልዎ የተሞላበትና ማንነትን የለየ ነው፤” በሚል የሚሟገቱም አሉ።

ስማቸው በምስጢር እንዲያዝ የጠየቁን ግለሰብ፣ በዐዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ ሥፍራዎች አንዱ በኾነው ለገዳዲ እና ለገጣፎ አካባቢ፣ ለ15 ዓመታት መኖራቸውን ይናገራሉ። ግለሰቡ ለዓመታት የኖሩበት ያ ቤት፣ ዛሬ፣ ለወትሮው ከቆመበት ሥፍራ እንደማይገኝ ገልጸዋል።

ሰሞነኛ አዳርና ውሎቸው፣ አንዴ በድንኳን፣ አልፎ አልፎ ደግሞ በኪራይ መጠለያ እንደኾነ አባወራው ያስረዳሉ። የዚኽ ምክንያቱ ደግሞ፣ የሠሩት ቤት፣ በአካባቢው አስተዳደር እንዲፈርስ መደረጉ ነው።

ሌላው አስተያየት ሰጪአችን ደግሞ፣ ከ13 ዓመታት በላይ የካ ጣፎ አካባቢ፣ “ከገበሬዎች ገዛኹት” ባሉት ይዞታ ላይ፣ ቤት ሠርተው ሲኖሩ እንደነበር ይናገራሉ። በመጋቢት ወር ግን ነገሮች መቀየራቸውን፣ ለአሜሪካ ድምፅ ያስረዳሉ።

በልዩ ልዩ አካባቢዎች ቤታቸው የፈረሰባቸውን ነዋሪዎች አነጋግረናል፤ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG