አዲስ አበባ —
ችግሩ በሰንጋፋ የተገነባው ዘመናዊ የቆሻሻ ማጠራቀምያ በአከባቢው አርሶ አደሮች ተቃውሞ ማንሳቱ ነው።
በአንዳንድ አከባቢዎች የሚታዩ የቆሻሻ ክምሮች በቤት በራፍ የሚስተዋሉ ክምችቶች ሰሞኑን የከተማዋ ችግሮች ሆነዋል። ነዋሪዎች ከየቤታቸው አልያም ከየግቢያቸው የሚሰበሰቡት ቆሻሻ ወደ በራፍ ሲያወጡ በየአከባቢው የተሰማሩ የጽዳት ሠራተኞች ይህን እያነሱ አንድ ቦታ ሲያከማቹ የተከማቸውም በመኪና ተጭኖ ሲወሰድ የተለመደ ተግባር ነበር ሰሞኑን ግን እነዚህ የጽዳት ሠራተኞች በመደበኛ ሥራቸው ላይ አልነበሩም።
ይህ የተሰበሰበው ቆሻሻ በፍጥነት ባለመነሳቱ የጤና ስጋት እየሆነባቸው መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።