በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ሰሜን ኮሪያና ኤርትራ ዜጎቻቸው ለዘመናዊ ባርነት መጋለጥ ቀዳሚዎች ተባሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዓለም ዙሪያ በዜጎቻቸው ለዘመናዊ ባርነት መጋለጥ አጋጣሚዎች ሰሜን ኮሪያ እና ኤርትራ ግንባር ቀደሞቹ ሀገሮች ናቸው ሲል ዛሬ ይፋ የተደረገ ዓለምቀፍ ጥናት አስታወቀ።

በዓለም ዙሪያ በዜጎቻቸው ለዘመናዊ ባርነት መጋለጥ አጋጣሚዎች ሰሜን ኮሪያ እና ኤርትራ ግንባር ቀደሞቹ ሀገሮች ናቸው ሲል ዛሬ ይፋ የተደረገ ዓለምቀፍ ጥናት አስታወቀ።

“ዘ ግሎባል ስሌቨሪ ኢንዴክስ” የዓለምቀፍ ባርነት ሰንጠረዥ የተባለው ድርጅት ባወጣው ሪፖርቱ እኤአ በ2016 በዓለም ዙሪያ ሰዎች በዘመናዊ ባርነት የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40.3 ሚሊዮን ይደርሳል ብሎ እንደሚገምት ገልጿል።

ድርጅቱ በግምገማው ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግዴታ የጉልበት ሥራ፣ የግዴታ ጋብቻ፣ ህጻናትን መሸጥና መበዝበዝን፣ የለየለት ባሪያ ፍንገላን በዘመናዊ ባሪያ ፍንገላነት ፈርጁዋል።

ከአሥር ሰው አንዱ በዘመናዊ ባርነት የተያዙ ያላት ሰሜን ኮሪያ ከህዝቧ ብዛት አኳያ በንጽጽር በሰንጠረዡ በአንደኝነት የፈረጃት ሲሆን የሚበዛው ህዝቧ በመንግሥት በግድ ተይዞ እንደሚሰራ ገልጹዋል፡፡

ከሰሜን ኮሪያና ኤርትራ ቀጥሎ ቡሩንዲ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ፣ አፍጋኒስታን፣ ሞሪታንያ፣ ደቡብ ሱዳን ይገኙባቸዋል።

የሰንጠረዡ ዓላማ ተጨባጭ መረጃ በማቅረብ መንግሥታት እና ኩባኒያዎች ችግሩን ለማስወገድ እንዲሰሩ ግፊት ለማድረግ መሆኑን ግሎባል ስሌቨሪ ኢንዴክስ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG