በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ 22ሺሕ የሱዳን ስደተኞች ወደ ዐዲስ መጠለያ እየተዛወሩ ነው


አሶሳ
አሶሳ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ 22ሺሕ የሱዳን ስደተኞች ወደ ዐዲስ መጠለያ እየተዛወሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በኩርሙክ ጊዜያዊ መጠለያዎች የነበሩ 22ሺሕ የሱዳን ስደተኞች፣ በዚያው ክልል ውስጥ ወደተዘጋጀ የኡራ ቋሚ መጠለያ እየተዛወሩ መኾናቸውን፣ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአገልግሎት ተቋሙ የአሶሳ ቅንርጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ያሲን አሸናፊ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ስደተኞቹ የነበሩበት የኩርሙክ ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ፣ ዓለም አቀፍ መስፈርትን እንደማያሟላ ጠቅሰው፣ ዐዲሱ የኡራ መጠለያ ጣቢያ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ አራት ሺሕ ስደተኞች ወደ ዐዲሱ መጠለያ መግባታቸውን የተናገሩት አቶ ያሲን፣ ቀሪዎቹ 18ሺሕ ስደተኞችም በ10 ቀናት ውስጥ ወደ መጠለያው ይጓጓዛሉ፤ ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG