ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
በምኅፃር ሲፒጄ እየተባለ የሚጠራው የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ኰሚቴ (Committee to Protect Journalists – CPJ)፣ በአሸባሪነት ተከሳ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ታሥራ ያለችው ጋዜጠኛና አስተማሪ ርዕዮት ዓለሙ ከማረሚያ ቤቱ ባለሥልጣናት “ወከባና ማስፈራራት ይደርስባታል” ሲል ስጋቱን አስታውቋል።
ሲፒጄ ይህን ስጋቱን የገለፀው ለኢትዮጵያው የፍትህ ሚኒስትር ብርሃን ኃይሉ በፃፈው ደብዳቤ ነው።
የርዕዮት ዓለሙ ሰብዓዊ መብቶች እየተጣሱ መሆናቸውን የገለፀው የሲፒጄ ደብዳቤ የጤንነቷ ሁኔታም ከቀን ወደ ቀን እያሽቆለቆለ የመሆኑ ነገር አሳሳቢ እንደሆነም አመልክቷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የአዲሱ አበበ ዘገባ ያዳምጡ፡፡